ዶ/ር ምንተስኖት
ማህተመስላሴ

የመካንነት እና IVF ሰብስፔሻሊስት| የማህፀንና የጽንስ ስፔሻሊስት| የኢንዶስኮፒክ ሰርጅን | ከ PCOS ጋር የተያያዘ የመካንነት ሕክምና | የ PCOS ክሊኒክ በኢትዮጵያ መሥራች

ከ 7+ ዓመት በላይ የመካንነት ሕክምና ልምድ

Dr. Mintesnot Mahtemesilassie
16+ ዓመት የሕክምና ልምድ

ስለ ዶ/ር ምንተስኖት

ልምድ


16+ ዓመት የሕክምና ልምድ

አይ ቪ ኤፍ እና የመካንነት ሕክምና


የመካንነት ሕክምና፣ የ IUI ሕክምና፣ የ IVF ሕክምና፣ የ PCOS ሕክምና እና የማኅፀን እና ፅንስ ችግሮች ሕክምና

የአገልግሎት መርሆዎች


ለእያንዳንዱ ታካሚ ልዩ ትኩረት በመስጠት፣ በሚስጥራዊ መንገድ አገልግሎት መስጠት

ትምህርት እና ሙያዊ ብቃቶች

  • ከ PCOS ጋር የተያያዘ ልዩ የመካንነት ሕክምና
  • የ PCOS የረጅም ጊዜ ክትትል እና አጠቃላይ እንክብካቤ
  • የሕክምና ዶክተር (MD)
  • የማህፀንና የጽንስ ሕክምና ስፔሻሊስት
  • የመካንነትና የIVF ሕክምና ሰብስፔሻሊስት
  • የኢንዶስኮፒክ (ላፓሮስኮፒክና ሂስቴሮስኮፒክ) ሰርጅን

የስራ ልምድ

  • በመካንነትና በIVF (REI) ሕክምና ከ7+ ዓመት
  • በማህፀንና በጽንስ ሕክምና ከ5+ ዓመት
  • የእናቶች እና ህፃናት ሕክምና መስራች (ራስ ደስታ ዳምጠው)

የሰሩባቸው ተቋማት

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
ጅማ ዩኒቨርሲቲ
ቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ
አሰላ ዩኒቨርሲቲ
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
ራስ ደስታ ዳምጠው መታሰቢያ ሆስፒታል (እናቶች እና ህፃናት ሕክምና መስራች)
ኒው ሊፍ ፈርቲሊቲ እና ሪፕሮዳክቲቭ ሴንተር

ልዩ የሙያ ብቃት

የPCOS/PMOS አጠቃላይ እንክብካቤ

ለPCOS/PMOS የረጅም ጊዜ ክትትል እና አጠቃላይ እንክብካቤ

ከPCOS ጋር የተያያዘ የመካንነት ሕክምና

የ PCOS በአዲስ ቀላል አነስተኛ ወጪ በሚጠይቅ ውጤታማ የመካንነት ሕክምና

የእንቁላል የማደግና የመለቀቅ ችግሮች

መደበኛ ያልሆነ የእንቁላል ማደግ እና መልቀቅ ችግር ላላቸው መፍትሔ መስጠት

ከታይሮይድ እና ፕሮላክቲን ሆርሞን ጋር የተያያዘ መካንነት

ከታይሮይድ እና ፕሮላክቲን ሆርሞን ጋር የተያያዘ መካንነት ቀላል መፍትሔ መስጠት

የወንድ መካንነት ምርመራና ሕክምና

የወንድ መካንነት ሙሉ ምርመራ እና የተሟላ ሕክምና

የሴት መካንነት ምርመራና ሕክምና

የሴት መካንነት ሙሉ የምርመራ እና የህክምና አገልግሎት

ዝቅተኛ የእንቁላል ክምችት

ዝቅተኛ እንቁላል ክምችት ላለባቸው ታካሚዎች ልዩ እንክብካቤ

እንደየታካሚው የእንቁላል ማነቃቂያ መስጠት

ለእያንዳንዱ ታካሚ በግል የተበጀ የእንቁላል ማነቃቂያ አገልግሎት

በማህፀን ውስጥ የዘር ማስገባት (IUI)

የወንድ ዘር ፍሬ አዘጋጅቶ ወደ ማኅፀን ውስጥ በቀጭን ቱቦ የማስገባት ሕክምና

አይ ቪ ኤፍ / ኢክሲ

የወንድ እና የሴት የዘር ፍሬን ዘመኑ ባፈራቸው ቴክኖሎጂዎች አዋህዶ ከ3-5 ቀናት ተንከባክቦ ወደ ማኅፀን ውስጥ የመመለስ ሕክምና

ተደጋጋሚ የዕርግዝና መቋረጥ (ውርጃ) ምርመራ እና ሕክምና

ተደጋጋሚ የዕርግዝና መቋረጥ ላለቸው መመርመር እና ማከም

የዘር እና የፅንስ ለረጅም ጊዜ አቀዝቅዞ የማስቀመጥ ሕክምና

የዘር ፍሬን ለወደፊት ለመጠቀም ወይም ከካንሰር ሕክምና ጋር ተያይዞ የሚመጣን መካንነት ለመከላከል ዘርን የማስቀመጥ ሕክምና

ቅድመ እና ድህረ ዕርግዝና ምክር

ለጥንዶች ከታቀደ ዕርግዝና በፊት የተሟላ የጤና ምርመራ እና ምክር መስጠት እንዲሁም ከወሊድ በኋላ የሚሰጡ የጤና እንክብካቤዎችን መስጠት

የጤና ምክሮች

መደበኛ የመካንነት ምርመራ ሁሉንም የመካንነት ምክንያቶች ላያሳይ ይችላል

መደበኛ የመካንነት ምርመራ ሁሉንም የመካንነት ምክንያቶች ላያሳይ ይችላል

በመደበኛ የመካንነት ምርመራ ሁሉንም የመካንነት ምክንያቶች ማወቅ ይቻላል ማለት አይደለም። ሁሉም ምርመራዎች ጥሩ ናቸው ቢባልም፣ አንዳንድ የመካንነት ምክንያቶች በአሁኑ ጊዜ በሕክምናው ዓለም ላይ ባሉ መደበኛ ምርመራዎች ላይ ላይታዩ ይችላሉ:: ስለዚህ፣ እርግዝና ካልተከሰተ፣ ውድ የሆነውን የመውለድ ጊዜዎን ሳያባክኑ፣ ከቀላል ወደ ውስብስብ የሚሰጡ የመካንነት ህክምናዎችን ደረጃ በደረጃ በትክክለኛ ባለሙያ እየተከታተሉ መሄድ ይመከራል።

የቪትሮ ፈርቲላይዜሽን (IVF) እውነታ፦ ከዕድሜ ጋር የሚቀያየር ስኬት

የቪትሮ ፈርቲላይዜሽን (IVF) እውነታ፦ ከዕድሜ ጋር የሚቀያየር ስኬት

ብዙ ጥንዶች አይ ቪ ኤፍ (IVF) በየትኛውም የዕድሜ ክልል ውስጥ ቢደረግ ሁልጊዜም ሙሉ በሙሉ ስኬታማ የሚሆን ይመስላቸዋል። ነገር ግን የIVF ሕክምና ስኬት በአብዛኛው የተመሠረተው በሴቷ የእንቁላል ጥራት እና ብዛት ላይ ሲሆን፣ ይህም ከዕድሜ መጨመር ጋር አብሮ የመቀነስ ባሕሪ አለው። በመሆኑም በተፈጥሮ መንገድ ለማርገዝ ከአንድ ዓመት በላይ (ወይም ዕድሜዎ ከ35 በላይ ከሆነ ከስድስት ወር በላይ) ከሞከሩና ካልተሳካ፣ ጊዜ ሳይወስዱ ወደ ስፔሻሊስት ጋር መቅረብ ወሳኝ ነው። የIVF ሕክምናን ቀድሞ መጀመር ጥራቱና ብዛቱ የተሻለ የእንቁላል ክምችት ለማግኘት ስለሚረዳ የፅንስ መፈጠር እና የመውለድ ዕድልን በከፍተኛ ደረጃ ያሳድጋል።

የመውለድ ዕድልን ማሳደግ፦ በዕለት ስሌት ላይ ብቻ አለመተማመን

የመውለድ ዕድልን ማሳደግ፦ በዕለት ስሌት ላይ ብቻ አለመተማመን

ብዙ ጥንዶች እርግዝና በሚፈጠርባቸው ቀናት(ከ12-16 ባሉት ቀናት) ብቻ ግንኙነት ማድረግ እርግዝናን በፍጥነት ለማግኘት ብቸኛው መንገድ እንደሆነ ያምናሉ። ነገር ግን፣ የፒሲኦኤስ (PCOS) ችግር፣ የእንቁላል ክምችት ማነስ ወይም መደበኛ ያልሆነ የወር አበባ ዑደት ያላቸው ሴቶች ከእነዚህ ቀናት ቀድመው ወይም ዘግይተው እንቁላል ሊያመርቱ ይችላሉ። እንቁላል ከተመረተ በኋላ በሕይወት መቆየት የሚችለው ለ12–24 ሰዓታት ብቻ በመሆኑ፣ በዕለት ስሌት ላይ ብቻ መተማመን ለፅንስ ዝግጁ የሆነውን ትክክለኛውን ቀን እንዲያመልጥዎት ሊያደርግ ይችላል። ስለዚህ፣ የተሻለ ውጤት ለማግኘት የየራሳቸውን የእንቁላል ማምረቻ ዕለት ማወቅ አስፈላጊ ሲሆን፤ ለዚህም ወደ ወሊድ ስፔሻሊስት ዘንድ በመሄድ በማህፀን አልትራሳውንድ (Transvaginal Ultrasound) ክትትል ማድረግ አስተማማኙ መንገድ ነው።

ጠቃሚ መረጃ

የማማከር ዓይነቶች

በ ድረ-ገጹ አማካኝነት በ አካል እንዲሁም በስልክ ዶክተሩን ለማማከር ቀጠሮ ይያዙ።

ሁለቱም አማራጮች ይገኛሉ። ታካሚዎች በስልክ (ለ20 ደቂቃ) ወይም በአካል በክሊኒኩ መጥተው ማማከር ይችላሉ።

ለማህበራዊ ሚዲያ እና ይዘት

የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች:

የክሊኒኩ መገኛ አድራሻ

ማዕዶት መካከለኛ ክሊኒክ ፤ አዲስ አበባ , ኢትዮጵያ

የማማከሪያ ቀጠሮ ይያዙ

ቅጹን ይሙሉ፤ አስተያየቶችን በቅርቡ ያገኛሉ።

⚠️
ይህ ቦታ የሚያገለግለው ድንገተኛ ላልሆኑ የጤና ማማከር ጥያቄዎች ብቻ ነው። አስቸኳይ የጤና እክል ካጋጠመዎት፣ እባክዎትን አሁኑኑ ወደ ህክምና ተቋም ይሂዱ።
ወንድ
ሴት
መረጃዎ ሙሉ በሙሉ በሚስጥር የተጠበቀ ነው።
የሚመለከትዎትን አንዱን ወይም ብዙዎቹን ይምረጡ።
ቅድመ-እርግዝና ምክር
የመካንነት / የመውለድ ችግር
የወር አበባ ጤና
የወር አበባን መዛባት በተመለከተ
የሆርሞን መዛባት ችግር
የወንዶች ሥነ-ተዋልዶ ጤና
የአባላዘር በሽታዎች (STIs)
የእርግዝና እና የድህረ-ወሊድ እንክብካቤ
የማህፀን ዕጢ (Fibroid) እና (PCOS)
የማህፀን በር ካንሰር ቅድመ-ምርመራ (Pap Smear)
ሌላ
×